Tender Detail

Tender Details

  • Company ብርሃን ኢንሹራንስ
  • Address , Phone: 0114704054
  • Website
  • Deadline01 Aug 2024, 9:42 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ብርሃን ኢንሹራንስ BERHAN INSURANCE ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ኢንሹራንስ


ብርሃን ኢንሹራንስ ኢማ ለ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች፣የህትመት ውጤቶች፣የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች (ቶነሮች)፣ኮምፒተሮችና ፕሪንቶሮች፣ የፅዳት ዕቃዎች በተጨማሪም ለዚሁ ዓመት የሚሆንየሰራተኞች የደንብ ልብስ ከታች በቀረቡት ምድብ መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ምድብ አንድ ፡-የፅህፈት መሳሪያዎች

ምድብ ሁለት ፡- የህትመት ውጤቶች

ምድብ ሶስት ፡- የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች (ቶነሮች)

ምድብ አራት - ኮምፒሮችና ፕሪንተሮች

ምድብ አምስት፡- የፅዳት ዕቃዎች

ምድብ ስድሰት፡- የሰራተኞች የደንብ ልብስ

በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለሚፈልጉት ምድብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ በኩባንያው ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በመክፈልየጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስም አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

4. ጨረታ ሰነዱን በፓስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአካል ተገኝተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ለተወዳደረበት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶችን፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞችን (ቶነሮች)፣የፅዳት ዕቃዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጨረታው ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡3ዐ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡

8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት

ወሎ ሰፈር ጋራድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ቢሮ ቁጥር 7

የሠው ኃይልና ንብረት አስተዳደር መምሪያ

ስልክ 0114674423/46 0114704054

Save Tender