የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ ግርማ አንበርብር እና በፍ/ባለዕዳ እነ ጌትነት አንበርብር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 183170 በ30/11/2010 ዓ.ም እና መ/ቁ 52623 በ29/10/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 በአሁኑ ወረዳ 4 የቤቁ 469 አዲስ ግምት የሆነ ቤት የቦታው ስፋት 208 ካ/ሜ በፕሮፖርሽን ቤቱ ካርታ ያለው መንገድ 1 ካሚ የሚነካው ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 14,394,060 (አስራ አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ስልሳ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ 2ኛ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 በአሁኑ ወረዳ 4 የቤ.ቁ 470 አዲስ የሆነ ቤት የቦታው ስፋት በፕሮፖርሽን 59 ካ/ሜ ቤቱ ካርታ ያለው መንገድ 1 ካ/ሜ የሚነካው ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,893,705 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ሶስት ሺ ሰባት መቶ አምስት ብር) ሆኖ ነሐሴ 29 ቀን 2016ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ጀምሮ የሚሸጥ ሲሆን የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፈደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክትሬት
