Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉምሩክ ኮሚሽን
  • Address , Phone: 00 00 00 00
  • Website
  • Deadline30 Jul 2024, 3:47 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ የቤት እቃ ፣ የቤት ማስዋቢያ ፣ ጫማዎች ፣ ምግብ ነክ ፣ ስፔርፓርት ፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

የጉምሩክ ኮሚሽን


የግልፅ እና የሀራጅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ የቤት እቃ ፣ የቤት ማስዋቢያ ፣ ጫማዎች ፣ ምግብ ነክ ፣ ስፔርፓርት ፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ የቀረቡትን እቃዎች በቀን 29/11/2016 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. ለግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ፣
  2. ለሀራጅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል ፤
  3. ለግልፅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛትየሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል ፤
  4. ለሃራጅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል ፤
  5. ለግልፅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፤
  6. ተጫራቹ በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በo5 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት ፤
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፤
  8. በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመሰስላቸዋል ፤
  9. ማንኛውም ተጫራች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) አሰርቶ ማምጣት አለበት ፤
  10. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን መሰረዝ ይችላል ፤
  11. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል ፤
  12. ተጫራቹ ዕቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም ፤
  13. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነድ በቀን 01/12/2016 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ እስከ 3:45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው 3:45 ተዘግቶ በቀን 01/12/2016 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ፤

የሀራጅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው የሚካሄደው በቀን 01/12/2016 ከረፋዱ 4፡30 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ፤

N.B፦ አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender