በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች የጠዋት እና ማታ ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ ከ12-15 ሰዎች መጫን የሚችል ሚኒባስ ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች የሰርቪስ የአገልግሎት ግዥ/ መግዛት ይፈልጋል
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ምስራቅ/ቅ/ፅ/ቤት 001/2017
በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች የጠዋት እና ማታ ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ ከ12-15 ሰዎች መጫን የሚችል ሚኒባስ ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች የሰርቪስ የአገልግሎት ግዥ/ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፣
- ሊብሬና የሶስተኛ ወገን ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 / አምስት ሺህ ብር / ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /C.PO/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር የጨረታው ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ በሻሌ ሳይት ውሃ ተንከር አካባቢ በፕሮጀክቱ ጽ/ቤቱ ህንጻ ቁጥር 13 ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሽያል ሠነዶች ተለይቶ በተለያየ ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናሻል ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኮፒ ተብሎ በአራት ፖስታ በማድረግ ኮፒ እና ኦርጅናሉ በጉልህ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ ከ2፡00-11፡00 ሰዓት ድረስ የጽ/ቤቱ ቢሮ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ /ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት/ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ከሰዓት 4፡30 ሰዓት በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ሲገኙ የአሸነፉባቸውን አገልግሎት የውል ማስከበሪያ ለማስያዝና ከመስሪያ ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት ለመፈፀም መስማማት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፦ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ በሻሌ ወረዳ 04 ውሃ ታንከር አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤታችን
ማብራሪያ፡- 0913-48-96-63/0911-06-33-70/0975-02-91-75 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
