የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሲጠቀምባቸው ከነበሩት የአይሲቲ ዕቃዎች እና የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ ሶፍትዌሮች የአገልግሎታቸው ጊዜያቸው እየተጠናቀቀ በመሆኑ አገልግሎቱ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ለማድረግ ICT equipment and cyber security software supply, Installation & Configuration መግዛት ይፈልጋል
Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
RE-FHC/NCB/PG/36/09/2016
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሲጠቀምባቸው ከነበሩት የአይሲቲ ዕቃዎች እና የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ ሶፍትዌሮች የአገልግሎታቸው ጊዜያቸው እየተጠናቀቀ በመሆኑ አገልግሎቱ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ለማድረግ ICT equipment and cyber security software supply, Installation & Configuration ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር RE-FHC/NCB/ PG/08/11/2016 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ለኮርፖሬሽኑ የአይሲቲ ዕቃዎች እና የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ ሶፍትዌሮች አቅርቦት ከነገጠማው ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ : በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት በወጣው የመንግሥት የግዥ አዋጅ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
- የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በተለምዶ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ወይም ነሐሴ 07 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን : ስም : ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትነሐሴ 07 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች የዕቃዎች ግዥ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና በቅርንጫ ጽ/ቤቶች ቅጥር ግቢ ያስረክባል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡ 011-855-36-17 ወይም
011-553-95-35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
