በአርሲ ዞን የዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2017 ዓ.ም በጀት የቢሮ ፈርኒቸሮች ፣ የፅዳት የፅህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ የኤሌክሮኒክስ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ፣ የተለያዩ የቴክኒከና ሙያ የስልጠና ዕቃዎች ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድረው መግዛት ይፈልጋል
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት የአርሲ ዞን የዲግሉና ጢጆ ወ/ገ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2017
በአርሲ ዞን የዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2017 ዓ.ም በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች ፣ የፅዳት የፅህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ የኤሌክሮኒክስ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የመኪናጎማዎች ፣ የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ የስልጠና ዕቃዎች ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድረው መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር በመክፈል ያሳደሱ።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4 በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉመሆን አለባቸው፡፡
5. አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
6. ዕቃዎቹን መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
7. አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋው በቁጥርና በፊደል መፃፍ አለባቸው፡፡ በቁጥርና በፊደል የተገለፀው የዋጋ መጠንመካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋመካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
8. ተወዳዳሪዎች ሀሳብ የሚቀርበው ሰነድ ላይ የዕቃው አይነት ፣ የምርቱ አይነት ፣ የተመረተበት አገር ፣ ሞዴልቁጥሩንና የተመረተበትን ዓ.ም ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት ይኖርበታል፡፡
9. ተወዳዳሪዎች ባሸነፉበት እቃ ላይ የእቃውን (ናሙና) ለአንድ ዕቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውንእንዲሁም ቀን ፊርማና የድርጅቱን ማሕተም ማስፈር ይገባቸዋል፡፡
11. መ/ቤቱ የግዥ መጠኑን በ20% ያህል መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፣
12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዲ/ጢጆ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት/ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራሰዓት ለያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ለጽህፈት መሣሪያዎች፣ ለመኪና ጎማዎች እናለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር20,000.00 (ሃያ ሺህ) ፤ እንዲሁም ፤ ለጽዳት እቃዎች ፣ እና የቴክኒከና ሙያ የስልጠና ዕቃዎችለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) ፣ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀባንክ በክፍያ ማዘዣ (CP.O.) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን ፋይናንሻል ዶከመንት ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴከኒካል ዶክመንትኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
15. ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውልመቀበል አለበት
16. አሸናፊው ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝይኖርባቸዋል፡፡
17. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናትየሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ከ4፡00 ሰዓትበኋላ የጨረታው ሳጥን ስለሚዘጋ በሰዓቱ ያልተገኘውን ተጫራች የማናወዳድር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
18. ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ ዓመት በዓል ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠመረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-338-0014፣ 09 10 001 453 ይደውሉ፡፡
በአርሲ ዞን የዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
