አዋሽ ባንክ አ.ማ የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ አ.ማ የተሻሻለው የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 ከመውጣቱ በፊት የውጭ ዜግነት ከያዙትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን የሚከተሉትን አክሲዮኖች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክባወጣው መመሪያ ቁጥር FlS/01/2016 መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
የጨረታምድብ(ሎት) |
ለጨረታ የቀረቡአክሲዮኖች ሰርተፍኬትቁጥር |
የአክሲዮኖቹብዛት
|
የአንዱ አክሲዮንመነሻ ዋጋ
|
የአክሲዮኖቹጠቅላላ መነሻዋጋ
|
|
1 |
20223 እና 0037992 |
180 |
1,000.00 |
180,000.00 |
|
2 |
24416 እና 24468 |
19 |
1,000.00 |
19,000.00 |
|
3 |
42865 እና 0035254 |
2 |
1,000.00 |
2,000.00 |
በመሆኑም፡-
- የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥርSBB/73/20 ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የውጭ ዜጎች እና ድርጅቶች በጨረታው በመሳተፍመግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታው ቀን በፊትከባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ብር 200 (ሁለት መቶ) ከፍለው በመውሰድ ቅጹን ሞልተውበኤንቨሎኘ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስከባንኩ ዋና መ/ቤት ጀርባ ባንኩ በተከራየው ኢያሜክስ ህንፃ የመሬት ወለል ላይ ባለው የባለአክሲዮኖችአገልግሎት ዋና ክፍል ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት ቦታ ህጋዊ ተጫራቾችወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን አክሲዮኖቹን ተጫርተው የሚገዙበትን ዋጋ ¼ (እሩቡን)በአዋሽ ባንክ ስም በተሠራ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ ጋር አያይዘው ማቅረብአለባቸው።
- ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች በቀረበ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- በአንድ ሎት (ምድብ) የቀረቡ አክሲዮኖችን ከፋፍሎ ዋጋ ማቅረብ መጫረት አይቻልም።
- ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድወይም ፓስፖርት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑየውጭ ዜጎች ደግሞ ቢጫ (የሎው) ካርድ እና ፓስፖርት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው በውጭ ምንዛሪ ብቻሲሆን ጨረታውን ካሸነፉም ክፍያ መፈፀም የሚቻለው ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሪ ብቻ ነው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀንጀምሮ በአምስት /5/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- ተለያይተው የቀረቡትን ሎቶች (ምድቦች) መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ምድብ(ሎት) በተለያየ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦውም ተለያይቶ መቅረብአለበት።
- በሌሎች ሕጎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጎች ተፈፃሚነት አላቸው።
- ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
“ይህ ማስታወቂያ እንዲተላለፍ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ማረጋገጫ አግኝቷል”
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115-57-00-92/0115571823
ፖ.ሣ.ቁ 12638
አዲስ አበባ
አዋሽ ባንክ
