የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ን/አስ/ቡድን በ2017 በጀት ዓመት በኤሌክትሪክ የሚሰራ የከተማ ባስ በግልፅ ጨረታ እወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል
የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ን/አስ/ቡድን በ2017 በጀት ዓመት በኤሌክትሪክ የሚሰራየከተማ ባስ በግልፅ ጨረታ እወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች
በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin number/ ያላቸው፣
- በግዥ መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡመሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የከተማ ባሱን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያትእዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደ/ብ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ቢሮ ቁ 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀንጀምሮ ለ30/ሰላሳ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ማስገባትይኖርባቸዋል፡፡ በዚህም ሰዓት ይታሸጋል፡፡ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ታዛቢዎች እናየውስጥ ኦዲተሮች በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በአከፋፈቱ ስነ-ስርዓት ላይባለመገኘታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 500 /አምስት መቶ ብር በመክፈል ከግዥና ን/አስ/ቡድን መውሰድይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ ግዥውን የሚፈጽሙ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው መሠረት በጥቅል በሎት ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘትወይም በስልክ ቁጥር 011 637 5610 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
