የG+2 የሆነ ሕንፃ (ቤት) የሐራጅ ሽያጭ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ መሀመድ ሰይድ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ሃያት ሙሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይየፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 253939 በ13/09/2013 ዓ.ም እና በመ/ቁ 191069 በ11/03/2013 ዓ.ምበዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ሩዋንዳ አካባቢ ውስጥ የሚገኝ ፓርሴል 7 በካርታ ቁጥር ቦሌ 9/15/1/11/22469/19347/01 የሆነ ካርታ ያለው በወ/ሮ መስታወት አማረ ማሞ ስምየተመዘገበ G+2 የሆነ ሕንፃ (ቤት) የይዞታው ስፋት 500 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,116,000(ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀምዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርትንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅትየንብረቱን ግምት ¼ ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነአሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊየሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬትንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወርግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን::
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
