ዎተርአክሽን WaterAction የጨረታ ማስታወቂያ ያገለገለ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር WACT/VD/001/24
ዎተርአክሽን WaterAction
ድርጅታችን ዎተር አክሽን ያገለገሉ መኪናዎችንና ሞተር ብስክሌቶችን በአሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥይፈልጋል፡ስለሆነም በጨረታዉ መካፈል የሚፈልግ ማንኛዉም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታዉ ላይ መወዳደርይችላል፡፡
1. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ከጠዋቱ 2፡ 30 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ከድርጅቱ ዋና መ/ ቤት ሂሳብክፍል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁትንያገለገሉ መኪናዎችን/ሞተር ብስክሌቶችንአ/ቃ/ክ/ከተማ ሽገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት 150 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘዉየኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክ፣ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የጥገና ማዕከል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት መኪና/ዎች/ሞተር ብስክሌት/ቶች የሚያቀርቡትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ዉስጥበተዘጋጀዉ “ያገለገሉ መኪናዎች/ሞተር ብስክሌቶች የጨረታ ሽያጭ የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ" ላይበመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ዉስጥ አስገብተዉ እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስማቅረብ ይችላሉ፡፡
4. አንድ ተጫራች መግዛት የሚፈልገዉ ከአንድ በላይ መኪና/ ሞተር ብስክሌት ከሆነ ለሚጫረተዉ ለእያንዳንዱመኪና/ ሞተር ብስክሌት በተናጠል የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መሙላት ይኖርበታል፡፡ አንድ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድየሚቀርበዉ ለአንድ መኪና/ሞተር ብስክሌት ብቻ ነዉ፡፡
5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ለሚጫረቱበት መኪና/ሞተር ብስክሌት የሚጫረቱበትን ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ (25%) በዎተር አክሽን ሥም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጨረታዉ ሰነድ ጋርገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታዉ ሐምሌ 25 ቀን 2016 4.3 ተዘግቶ በዚያዉ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ጨረታዉን ላሸነፉት ከዋጋዉ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን፣ጨረታዉን ላላሸነፉት የጨረታዉ ዉጤት እንደታወቀ ይመለስላቸዋል፡፡
8. የጨረታዉ አሸናፊ/ዎች ቀሪዉን ገንዘብ በአምስት (5) ቀናት ዉስጥ አጠቃለዉ ከፍለዉ ንብረቱን የማንሳት ግዴታአለባቸዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ዉስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ከፍለዉ ንብረቱን የማያነሱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታዉ ይሰረዛሉ፡፡
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ከአገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሕጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻ
ዎተር አክሽን
ለም ሆቴል አካባቢ ኖክ ነዳጅ ማደያ ትይዩ በስተደቡብ
250 ሜትር ወረድ ብሎ፣
(ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደዉ ዋና መንገድ ከመሬት
አስተዳደር አለፍ ብሎ ወደቀኝ በሚያስገባዉ አስፋልት
መንገድ)፤
ስልክ ቁጥር 011 663 1789/90፣ 011662 3318
ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 04 የቤት ቁ.144
አዲስ አበባ
