ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት Exhibition Center and Market Development Enterprise የጨረታ ማስታወቂያ
የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት ሂሣብን በባለሙያ ለማስመርመር በግልጽጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ መረጃ የያዘውን ሠነድ ከሐምሌ 08/2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ምድረስ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መስቀል አደባባይ በሚገኝው በኤግዝቢሽንማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት በመምጣት ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ሞልተው ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-8፡30 ድረስ በማዕከሉ የመሠብሠቢያአዳራሽ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በዚሁ ዕለት ማለትም ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡35 ላይ በማዕከሉ መሰብሰቢያአዳራሽ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ:-0912-01-73-78/0911-72-80-58/0115-15-16-99 ላይ መደወል ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
