የጉለሌ ክ/ከተማ ወ6/ ፋይናንስ ጽ/ቤት የካፍቴሪያ እና የመስተንግዶ አገልግሎት ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ፣ የቢሮ እድሳት አገልግሎት ፣ የህትመት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 001/2017
1. የካፍቴሪያ እና የመስተንግዶ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 75,875.00 ብር
2. የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 17,200.00 ብር
3. የቢሮ እድሳት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 30,000.00 ብር
4. የህትመት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6000.00 ብር
በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች፡-
- በጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በስማቸው ያላቸውን የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ግዴታቸውን በግብር አስገቢ በባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ
- ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN number/ VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው። ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ በብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ኦርጅናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ስም ማህተም ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት። የሚጫረቱበትን የዕቃ አይነት በመጥቀስ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በስራ ሰዓት በቢሮ ቁጥር 14 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ባበቃ በመጨረሻ ቀን 10፡30 ይታሸግና እና በማግስቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ማስያዝ አለባቸው። እና የጨረታውን አሸናፍፊ 10% የጨረታው ውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡30 ንብረቶችን በራሱ ማጓጓዝ ማስጫኛና ማውረጃውን ጨምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ ማውረድ ይኖርበታል።
- ጽ/ቤቱ የሚያጫርተውን የዕቃ ብዛት 20 ፐርሰንት መቀነስና መጨመር ይቻላል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጫራቾች ማብራሪያ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0111-22-67-04 እና 0118-12-24-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ማቅረብ የማይችል ከሆነ ገላጭ እስፔስፍከሽን ማምጣት አሊያም እቃውን የሚያሳይ ጥራት ያለው ማምጣት ይኖርባቸዋል።
- ለሰራተኛ ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጠው ጉ/ክ/ከ/ወ6 /አስተዳደር በሚገኝበት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የሰራተኞች ከበብ ሆኖ የቤት ኪራይ ወጪ የመብራት እንዲሁም የውሃ ወጪን ጨምሮ በመስርያቤቱ የሚሸፈን መሆኑን ያሳውቃል።
- አድራሻ ፡- ሽሮሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፊያ 500 ሜትር ገባ ብሎ
የጉለሌ ክ/ከተማ ወ6/ ፋይናንስ ጽ/ቤት
