Tender Detail

Tender Details

  • Company SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
  • Address ሀዋሳ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461228084
  • Website
  • Deadline30 Jul 2024, 4:24 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል እህል ለመግዛት በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች በድጋሚ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎

የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል እህል ለመግዛት በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች በድጋሚ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡- 

  1. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። 
  2. በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። 
  3. በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን እህል ለ6 ወራት የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
  4. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 12 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ሳጥን የሚታሸገው በአስራ ሁለተኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ሲሆን የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይሆናል ፤ ይህ ቀን የበዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
  8. ማንኛውም ተጫራች የእህል ናሙና ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ኮሚቴ ማሳየት አለበት።
  9. ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-122-80-84 መደወል ይችላሉ ።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም

 

Save Tender