የጨረታ ማስታወቂያ
ቶታል ኢነርጂስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንጋፋ ከሆኑትና በነዳጅ፣ በተፈጥሮ ጋዝ እና በዝቅተኛ ካርቦን ኤሌክትሪሲቲ ሽያጭ ላይየተሰማራ ኩባንያ ሲሆን በዓለማችን በ13ዐ አገራት ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ቶታልኢነርጂስ በኢትዮጵያ ውስጥ እ.ኤ.አ. ከ195ዐ ዓ.ም. ጀምሮና ከ17 ዓመት በፊትም ከሞቢል ኢስት አፍሪካ ውህደትበጠቅላላው በመላው ሀገሪቱ ከ143 በላይ በሆኑ ነዳጅ ማደያዎችና 5 የነዳጅ ማከማቻ ዴፖዎች ሃላፊነት በተሞላው መንገድየሽያጭ እና የአገልግሎት አሰጣጥን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. በሀገሪቱካሉት እና መሪ ከሆኑት የነዳጅ ኩባንያዎች አንዱ በመሆን በነዳጅና በዘይት ሽያጭ ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ጠመንጃ ያዥ ቶታልኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ የሚገኙትን የመኪና ማጠቢያ እና የጎማአገልግሎት መስጫ ቦታዎች አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
► ለመወዳደር የሚፈልጉ አመልካች ግለሰቦች፤
1. በትምህርት ደረጃቸው ቢያንስ 1ዐኛ ክፍልን ያጠናቀቁና
የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ከላይ የተጠቀሰዉ ሥራ የሚጠይቀውን የመሥሪያ ካፒታል /ገንዘብ/ በግላቸው የማቅረብ አቅም ያላቸው፣
3. ወቅታዊ የሆነና ያለፉትን 6 ወራት የሚያሳይ pod የተረጋገጠ የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ከባንኩየማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት የሚችሉ፣
4. የዕለት ተዕለት ሥራ በቂ ጊዜ ሰጥተው በግላቸው መምራት የሚችሉና፣ በስራው እንዲሁም በደንበኛ አያያዝ ጥሩ የስራልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
5. አመልካቾች ነዳጅ ማደያው የሚገኝበት ከተማ ወይንም አካባቢ ነዋሪ መሆን አለባቸው፣
6. ጊዜው ያላለፈበትና ተቀባይነት ያለው መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ማቅረብ የሚችሉ፣
► ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች፤
1. የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በስራሰዓት ሙለጌ ህንፃ ሰባተኛ ፎቅ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን የሽያጭ ቢሮ በመገኘት የማመልከቻ ሰነዱን ገዝተውና ሞልተውመመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ የማመልከቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
3. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
‣ ከማመልከቻ ሰነድዎ ጋር የሚከተሉት ደጋፊ መረጃዎች አባሪ መደረጋቸውን አይዘንጉ፤
1. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፣
2. ያለዎትን የገንዘብ አቅም ለማሳየት እንዲቻል ወቅታዊ የሆነ ቢያንስ የ6 ወር ተቀማጭ/ተንቀሳቃሽ ሂሳብዎን የሚገልጽየባንክ እስቴትመንትና የባንክ የማረጋገጫ ደብዳቤ፣
3. የትምህርት ደረጃዎን የሚያሳይ የተሟላ የትምህርት መረጃ ፎቶ ኮፒ፣
4. ያለዎትን ንብረት የገንዘብ አቅም ለማሳየት እንዲቻል ወቅታዊ የሆነ የቋሚ የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥሮች - 011 465 11 25 / 011 4 65 45 25 ይጠይቁ፡፡
ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር
