በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾችለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ % (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይምሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራአምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎበጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናትውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ስዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ :: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበትይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎችይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተውየመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ንብረቱን በሥራ ስዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሽረንደስላሴ ከተማ፣ ቀበሌ 04፣ አደባባይ ኃየሎምበሚገኘው የባንኩ ሽረንደስላሴ ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-515-11-53 እና 011-515-07-11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
|
የተበዳሪውስም |
የመያዣሰጪውስም |
የንብረቱ አይነት እናአገልግሎት| |
የቦታው ስፋትበካ.ሜ |
የባለቤትነትማረጋገጫ ካርታ |
ንብረቱየሚገኝበት| አድራሻ |
የጨረታውመነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታውየሚካሄድበትቀን |
የምዝገባሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
|
ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ወ/ሮአስመረትመለስወ/ ጊዮርጊስ |
G+2 መኖሪያቤት |
175 |
10306/5135/2012 |
በትግራይብ/ክ/ መንግስት፣ሽሬ ከተማ፣ቀበሌ
|
10,986,060.21 |
ነሐሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም |
4፡30_5፡30 |
5:30-6:00 |
