ቡና ባንክ አ.ማ የመኪና የሐራጅ ማስታወቂያ
ቡና ባንክ አ.ማ
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፣ ቡባ/ሕአዳ/ሐራጅ / 028/2016
ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የተመለከተውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረትአስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የመያዣ አይነት/ሞዴል |
የሻንሲ ቁጥር/ሴሪያል ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚከናወንበት |
ጨረታውየወጣው |
|
|
ቀን |
ሰዓት |
||||||||||
|
1 |
አቶ አብይኣማረ ዋሴ |
ተበዳሪ |
ጎጃም በረንዳ |
ሥከ-LD-1938 |
2015 ዊልሎደር |
CXG00953H001E0299 |
D9143009320 |
3,000,000.00 |
ሐምሌ 23 ቀን2016 ዓ.ም |
4:00-5:00
|
ለሁለተኛጊዜ |
የሐራጅ ደንቦች፣
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በቡና ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ መከፈል አለበት፡፡ ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ፡፡ ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
4. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
5. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፤ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
6. በሐራጁ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለማየት ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር በመነጋገር ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
8. ጨረታው በቡና ባንክ አማ ዋናው መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ፤ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ወደ ቦሌ ሲሄዱ ሩዋንዳ መታጠፊያ ሳይደርሱ በሚገኘው የባንኩ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ የሚከናወን ይሆናል፡፡
9. ባንኩ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፣ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስ.ቁ 011-1-58-08-63/011-1-26-36-09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
