ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2016 በጀት ዓመት በቁጥር 100 ከባድ ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል GPS ተከላ ፣ የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እስካነር እና የመሳሰሉት መገልገያ ማሽኖች ፣ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች ግዥ እና የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እስካነር እና የመሳሰሉት መገልገያ ማሽኖች ጥገና ለማከናወን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
የGPS ተከላ፣ የኤሌክትሮኒክስ ማሽኖች፣ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች ግዥ እና የኤሌክትሮኒክስ ማሽኖች ጥገና ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን በ2016 በጀት ዓመት በቁጥር 100 ከባድ ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል GPS ተከላ ግዥ፣ የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እስካነር እና የመሳሰሉት መገልገያ ማሽኖች ግዥ፣ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች ግዥ እና የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እስካነር እና የመሳሰሉት መገልገያ ማሽኖች ጥገና ለማከናወን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና በእቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና ቫት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፤ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥበሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራታቸው የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ለሎት I (GPS ተከላ) ብር 300 (ሶስት መቶ ብር)፤ ለሎት II (የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ፋክስ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እስካነር እና የመሳሰሉት መገልገያ ማሽኖች ግዥ) ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/፣ ለሎት III (የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች) ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እና ለሎት IV (የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ እስካነር እና የመሳሰሉት መገልገያ ማሽኖች ጥገና) ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር/ በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በየሎቱ በቀረበው የዕቃ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (Unit price)እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋ (Total Price) በግልፅ በማስቀመጥ ከነቫቱ ተ.እ.ታ ጨምሮ በመሙላት እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመጥቀስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሎት I ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፤ ለሎት II ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፤ ለሎት III ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) እና ለሎት IV ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾችወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታው ቀን የስራቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
በስልክ ቁጥር:- 011-4-39-00-75/35-92/15-69/011-4-39-10-27
ፋክስ ቁጥር ፡- 011-4-39 63-36/ 011-4-74-71-41 ፖ.ሳ.ቁ 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ሽገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት 70 ሜትር ገባ ብሎ
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
