Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Jul 2024, 4:08 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር SSNT-T470


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ ፡ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና የመንገድ ስራ ተቋራጮችን(GC/RC-1) በጨረታ አወዳድሮ የኮምቦልቻ አየር መንገድ ፕሮጀክት የዲዛይን ግምገማ፣ የግንባታ ቁጥጥር እናየኮንትራት አስተዳደር አገልግሎቶች (design Review, Construction Supervision and Contract Administration Services for Kombolcha Airfield Project) ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የታደሰ የምዝገባ ምስክርወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC-1 ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸውማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁለት (2) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ ተጫራቾች የእያንዳንዱፕሮጀክት አፈፃፀም ከ70% በታች ከሆነ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸውከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T470 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢ-ሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይምለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ማክሰኞ ነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

- ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:30 ሰዓት ገ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሴ አስም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር፡- 011-517-40-28

ኢ-ሜይል: AddisGEW@ethiopianairlines.com

አዲስ ገብረኪዳን

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ

Save Tender