የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ፡ _ SSNT-T-465
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው ቅጥር ግቢ ውስጥየተርሚናል እድሳት፣ የአውሮፕላን መንደርደሪያ እና ተጨማሪ መገልገያዎች ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀከት (Design-Build of Asosa Airport Terminal Renovation, Runway Strip and Ancillary Facilities Construction Project) የህንጻ ተቋራጭተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል። የፕሮጀከቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ270 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ ይሆናል፣ ስለሆነምከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች፣ አስፈላጊውን የሰው ሃይል፣ ማሽንና የግንባታ ግብዓት ማሟላት የሚችሉ ሥራተቋራጮች ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ ለመስራት ለ2016 ዓ.ም /2023/2024 እ.ኤ.አ. ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
2. በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁለት (2) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ ተጫራቾች የእያንዳንዱ ፕሮጀክትአፈፃፀም ከ70% በታች ከሆነ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም፡፡
3. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2016 ዓ.ም የተሰጠው፣
4. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል 12023/2024 G.C /2016 ዓ.ም የታደሰጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC/BC-1 የሆነ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
5. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል፣
6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
7. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
8. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜውያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
9. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝየኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T465 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍልበኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
10. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500.000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው።ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና Conditional የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለአንድ መቶ ሃምሳ (150) የቀን መቁጠሪያ ቀናት የጸና ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል እስከ ነሐሴ 07 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
13. አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011517 8953 ጠደሜ ተሰጋ
ኢ_ሜይል : TeymeT@ethiopianairlines.com
