በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 47/2016
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ፣ ሞባይሎች ፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች ፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልጽና በሃራጅ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐምሌ 04 ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም
- በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዕቃውን የግልጽና የሀራጅ ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CuSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ
|
የቅ/ፅ/ቤቱ ስም
|
የጨረታው አይነት
|
የንብረትመመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድከወሰዱ ቀን ጀምሮ
|
የጨረታውየመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንናሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክቅ/ፅ/ቤት
|
የዕቃ ሃራጅ
|
እስከ 08/11/2016
|
09/11/2016 4:00 ሰዓት ጀምሮይካሄዳል |
|
የዕቃ ግልፅ
|
እስከ 09/11/2016 |
10/11/2016 3:45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን4፡00 ሰዓትይከፈታል |
7. የጨረታው መክፈቻ ቦታ ፡- ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
8. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011 - 470 - 85 03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
