የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ልዩ ልዩ ቆርቆሮና ብረት ነክ አሮጌ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የልዩ ልዩ ንብረት ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ልዩ ልዩ ቆርቆሮና ብረት ነክ አሮጌ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ንብረቶቹም በኮሪደር ልማትና በከተማ ማደስ ፕሮግራም ምክንያት ከሚጠገኑና ከሚታደሱ ሕንፃዎችና ቤቶች የሚገኝ ንቃይ ቆርቆሮና ኤጋ ሽት በርና መስኮት እንዲሁም ሻተርና መሰል ልዩ ልዩ አሮጌ እቃዎች ናቸው።
መሥፈርት
1. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሠንጠረዡ ላይ በተሰጠው ትይዩ ባዶ ቦታ ላይ ብቻ ማስቀመጥ አለበት።
2. ድርጅቱ ለሽያጭ ያቀረብነውን ዕቃ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡ዐዐ ዕቃውን ፒያሳ በሚገኘው ዘውዲቱ ሕንጻ ግቢ በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) ከፍሎ ሠነዱን በመሙላት በኢንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ በድርጅቱ ጽ/ቤት ለዚሁ አለማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
3. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::
4. ተጫራቾች ሲወዳደሩ ለሚጫረቱበት ንብረት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር5,ዐዐዐ.00 (አምስት ሺህ ብር) በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(CPO) ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በ1ዐኛው ቀን ከቀኑ 1ዐ፡ዐዐ ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡ዐዐ ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል።
6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ
በስ.ቁ. 0111 55 86 80 ወይም 0111-57-47-99
በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ።
