የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ አያለው ገላ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ዘሀራ የሱፍ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 15993 በ8/8/2016 ዓ.ም እና በመ/ቁ 161448 በ7/9/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ሆዴሳ ወረዳ ብሎክ 141 የቤቁ 141/28 በወ/ሮ አሚና ሰይድ ስም ተመዝግቦ ያለው ኮንዶሚንየም ቤት ፍርድ ያረፈበት ቤት በቁጥር አ/ቃ/912/15/62850/00 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቤቱ ስፋት 28.73 ካ/ሜ የቦታው ስፋት በፕሮፖርሽን 19.82 ካ/ሜ ቤቱ እስቲዲዮ መሆኑ ታውቆ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 654,417.70(ስድስት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ አራት መቶ አስራ ሰባት ከሰባ ሳንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶCPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
