የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DCDF 001/2017
የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ገራውንድ ላይ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDF 001/2017
ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ ሹፌሩን ጨምሮ ከ12-15 ሰዎች እና ከዚያበላይ የመጫን አቅም ያላቸው ሞዴል 2000 እና ከዚያ በላይ ተሸከርካሪ/መኪና ብዛት አራት(04) በግልጽ ጨረታአወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት፡-
- ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር(TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች ግብር የመክፈልግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍየሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበትጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀንይተላለፋል::
- የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር)ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ከሰኔ 30/2016 እስከ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሐምሌ 15/2016 ዓ.ምከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጭን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውበአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም::
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት
የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ገራውንድ ላይ
