ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር HP/0005/16
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር HP/0005/16
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አግሮ ክላስተር ስር የሚተዳደረው ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር በስሩ ከሚያስተዳድራቸው በጅማ ዋናው ቢሮ እና በስምንት እርሻዎች የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ውድቅዳቂ ብረታብረቶች፣ የተሸከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች
የተዘረዘሩትን በሟማላት መጫረት ይችላሉ::
1. ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ሰነዱ ጋር በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ቫት ሰረተፊኬት ማቅረብ አለበት::
2. ያገለገሉ ዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘውን በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በአካል በመቅረብመግዛት ይችላሉ::
3. የመጫረቻ ሰነዶች ማንኛውም ለውጥም ሆነ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም::
4. ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር/HORIZON PLANTATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. /CPO/ ብቻ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው::
5. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል::
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
7. ጨረታው ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
አድራሻ ፡- ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር አዲስ አበባ መካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን አለፍ ቢሎ በሚገኘው ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት ሳራ ቅርንጫፍ ጎን
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0911899634 /0912171333 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
