Tender Detail

Tender Details

  • Company AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)
  • Address ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116 637485
  • Websitehttps://africainsurancesc.com/
  • Deadline05 Jul 2024, 12:06 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳትና ሪፍሬሽመንት እቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)


አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም
የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎
የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ቁጥር AIC - 0001/2024-25

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳትና ሪፍሬሽመንት እቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  •  ሀ. ሎት-1 የፅህፈት መሣሪያዎች
  • ለ. ሎት-2 የፅዳትና ሪፍሬሽመንት እቃዎች
  • ሐ ሎት-3 የህትመት ውጤቶች

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡ 

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ኩባንያው ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ
    አይሆንም፡፡
  3. በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሠነዱን ገዝተው የሚወዳደሩበትን ዕቃ ዓይነት እና ብዛት የሚገልፅ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በስራ ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከሐምሌ 01 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 05 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በሥራ ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ሐምሌ 05 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነድ የእቃዉ ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ እንዲሁም በሚያቀርቡት ናሙና (Sample) ላይ የድርጅታቸው ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
  8. አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው የሚያሳግድ ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሣሪያ ፣ የሪፍሬሽመንት እና የፅዳት እቃዎችን ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ እንዲሁም ለህትመት ውጤቶች ከ15 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሠረት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፅህፈት መሣሪያዎች እና የሪፍሬሽመንትና የዕዳት እቃዎችን ሲወዳደሩ ባስገቡት (ባቀረቡት) ናሙና እንዲሁም የህትመት ውጤቶቹ በኩባንያው ናሙና መሰረት መሆን አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች የኩባንያው ዋና መ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ኩባንያው ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0116 611877 / 0116 637485/ 0116 637716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ

Save Tender