ወጋገን ባንክ አ.ማ. አክሲዮን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ወጋገን ባንክ አ.ማ. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት የውጪ አገርዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን ብር 131,000.00 ዋጋ ያላቸውን 131 አክሲዮኖች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነምበጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥየመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በማቅረብ መጫረት ይችላሉ::
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፡-
- በጨረታው ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በመሳተፍ መግዛት ይችላል::
- የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1,000 (አንድ ሺ) ነው::
- ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ራስ መኮንን ጐዳና፤አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 21ኛ ፎቅ አክስዮን ክፍል በመገኘትከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ብር 50 (ሃምሳ) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ:: ተጫራቾች የዋጋ ማቅረብያ ቅፁን በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ አክሲዮን ክፍል በሚገኘው ሰነድመቀበያ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውናየሚመለከታቸው ታዛቢዎች በሚገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱትን አክሲዮኖች የመነሻ ጥቅል ዋጋ 1/4 በባንክ በተረጋገጠሲፒኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- አንድ ተጫራች ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም::
- ተጫራቾች ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ፣ ፖስፖርት ወይምተቀባይነት ያለው ሌላ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ሲኖርባቸው ተጫራቾች ድርጅቶች ደግሞ የመመሥረቻጽሑፍ ወይም ተቀባይነት ያለው ሰነድ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀንጀምሮ በአስራ አምስት(15) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው:: በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የማይደረግ ይሆናል::
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ ለባንኩ ያሲያዙት የጨረታ ዋስትና ወዲያውኑተመላሽ ይደረግላቸዋል፣
- በሌሎች ሕጐችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጐች ተፈፃሚነት አላቸው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-58 16 35 ይደውሉ::
Excelling Together
ወጋገን ባንክ አ.ማ.
