የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና የመንገድ ስራ ተቋራጮችን (GC/RC-1) በጨረታ አወዳድሮ የአርባ ምንጭ ኤርፖርት የአየር ማረፊያ እና ተርሚናል ጥገና ፕሮጀክት በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት ለማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-1468
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና የመንገድ ስራ ተቋራጮችን (GC/RC-1) በጨረታ አወዳድሮ የአርባ ምንጭ ኤርፖርት የአየር ማረፊያ እና ተርሚናል ጥገና ፕሮጀክት (Arba Minch Airport Airfield Maintenance Project) በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት (Design and Build Project Delivery Method) ለማሰራት ይፈልጋል::
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC- 1፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
አፈፃፀማቸው ከሰባ በመቶ በታች የሆነ (<70%) ከሁለት (2) በላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሮጄክቶች ያላቸው ተቋራጮች በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ብቁ አይደሉም።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT T468 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ዓርብ, ነሐሴ 03 2016 ዓ.ም ከ ቀኑ 08:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከ ቀኑ በ 09:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ:-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: KidistTa@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
