ገቢዎች ሚኒስቴር የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ ቴሌቭዥኖች ሌሎች የሆቴል ተጓዳኝ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር ዕዳ የያዛቸውን ተሽከርከሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶች ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር -08/2016
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 4 ተሠጠው ስልጣን መሠረትፍሩቲ ጁስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ፣የኢም ስሎው ጂን እስቴት ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እናከብሪህንጎ ኢንተርናሽናል አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
- የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች እና
- ከኤፍ ኬ ዲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ቴሌቭዝኖች፣ እስፒከር፣የሆቴል ጠረጴዛዎችና ሌሎች ተጓዳኝ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ(ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞእስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ህንፃ “ለ” 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 ከግዥና ፋይናንስአስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ” 2ኛ ፎቅቢሮ ቁጥር 20 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ ኛውን ብቻ ለጨረታማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Minstry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን |
የጨረታውየመዝጊያ እናየመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ገቢዎችሚኒስቴር
|
የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ ቴሌቭዥኖች ሌሎች የሆቴል ተጓዳኝዕቃዎች |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀበኋላ ቀጥሎ ባለው16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀንበ4፡00 ሰዓት |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ሀዊወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል ፡፡
6. የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታመክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
7 ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደአስፈላጊነቱ የሚታስብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶእንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላችዋል።
8 የተሸከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች(የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትንጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾችየግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-617-84-90 ኮድ(2044)(2045) (2046) የውስጥ መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል፡፡
ገቢዎች ሚኒስቴር
