የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች ሊፍት ፖኔል ሮቶ ብርቶች የሐራጅ ሽያጭ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ኤም ቢ ጥበቃ አገልግሎት እና በፍ/ባለዕዳ ክቡር ፍጥረት ኮንስትራክሽን መካከል ስላለው የፍርድአፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 311482 በ7/2/2016 ዓ.ም እና መ/ቁ 315393 በ10/8/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤቁ ቀጠና ቱርፍቱሳይት የሚገኙ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች ሊፍት ፖኔል ሮቶ ብርቶች የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 224,850 (ሁለት መቶሃያ አራት ሺ ስምንት መቶ ሀምሳ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረበ ተጫራቾችተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀምዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርትንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅትየንብረቱን ግምት ¼ ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነውግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስምየማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
