ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 003/2016 ዓ/ም
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ አንድ አርድቶፕ እና አንድ ፓራዶ በድምሩ 2/ሁለት/ መኪናዎች መግዛትስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች እያንዳንዱ ተጫራች እንዲያከብር ያስፈልጋል።
ስስዚህ በጨረታው ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
4. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከነ እስከ 4 የተጠቀሱትንና ሌሎች ጠቃሚ ናቸው የሚላቸውንማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ንብረቶቹ በአቅራቢው ድርጅት ወይም ተጫራች ግለሰብ እስቶክ የሚገኝ መሆኑና ውል ከተገባ በኋላ በ10 ቀናትውስጥ ማቅረብ አለበት፤
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራቀናት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና የንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የቢሮ ቁጥር 60 ቀርቦየማይመለስ ብር 400.00 ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የገንዘብ መጠን ወይም ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክበተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪውን ስምና አድራሻ የሚያመለክት /ሕጋዊ/ ወኪል የፈረመበትየተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸው በሰም በታሸገ ፖስታ ኤንቨሎፕ ማድረግ አለባቸው፡፡
11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡
0475511468/0917804727
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
