Tender Detail

Tender Details

  • Deadline30 Jul 2024, 3:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ሽያጭ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎

በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ዝናሽ ዳዲ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ብዙነህ ዳዲ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 181065 በ24/2/2015 ዓ.ም በ7/3/2015 ዓ.ም እና በመ/ቁ 186458 በ30/5/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤ.ቁ. 498 የሆነው የቦታው ስፋት 138 ካ/ሜ ይዞታ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ አቶ ፋስካ ዳዲ የሰሩት ሁለት ደጃፍ ብሎኬት የተሰራ ቤት የግላቸው ሲሆን ከዚህ ውጭ ያለው ስፋቱ 58.78 ካ/ሜ ቤትና ባዶ ቦታ አጠቃላይ በካርታ ቁጥር የካ/177472/05 በአቶ ዳዲ ያደቴ ስም የተመዘገበ ንፅፅር ካርታ ያለው አቶ ፋስካ ዳዲ የሰሩት ሁለት ደጃፍ በብሎኬት የተሰራ ቤት እንደማይሸጥ በካርታ ላይ የተመለከተው የቤት ቁ. 499 የቀበሌ ቤት መንገድ ልማት የፈረሰ መሆኑ ታውቆ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 9,956,322 (ዘጠኝ ሚሊዬን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አይካፈልም፡፡ በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፤ የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender