የጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ.የተ.የግል ማህበር የቢራ ገብስ እና የተመረተ ብቅል በጎተራ እና በመጋዘን ለረዥም ጊዜ ስለሚያከማች በነቀዝና መሰል ተባይ እንዳይጠቃ የጸረ ተባይ ኬሚካሉን ድርጅታችን የሚያቀርብ ሆኖ ለአንድ አመት የመከላከል አገልግሎት የሚሰጠውን ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
የጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ.የተ.የግል ማህበር
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የቢራ ገብስ እና የተመረተ ብቅል በጎተራ እና በመጋዘን ለረዥም ጊዜ ስለሚያከማች በነቀዝና መሰልተባይ እንዳይጠቃ የጸረ ተባይ ኬሚካሉን ድርጅታችን የሚያቀርብ ሆኖ ለአንድ አመት የመከላከል አገልግሎትየሚሰጠውን ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርትበጥንቃቄ በማንበብ እንድትወዳደሩ በአክብሮት እንጋብዛለን፤
- የታደሰ ህጋዊ የንግድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- በፀረ ተባይ መከላከል የስራ ዘርፍ የተሰማራ መሆን አለበት፤
- ተጫራቾች በጨረታለመሳተፍ ከላይ በቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትን እናየሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታና የጎተራ ብዛት ከዚህ ጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ሲሆን አገልግሎቱ ለአንድዓመት የሚቆይ ይሆናል፤
- የሰራተኛ ወጪ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት የባለሙያ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክየተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በፋብሪካው ፋይናንስመምሪያ ገ/ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላል፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፋብሪካው ንግድ መምሪያ ግዥ ክፍልቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ከ29/10/2016 እስከ 18/11/2016 ዓ.ም 5.00 ሰዓትድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት በጎንደር ብቅል ፋብሪካ የስብሰባ አዳራሽ በ18/11/2016 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ5፡00 ሰዓትይከፈታል፣
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከፋብሪካው ንግድ መምሪያ ግዥክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 00 09/ 09 13 59 85 63 / 09 18 06 41 75 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤
የጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ.የተ.የግል ማህበር
