ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የገዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
1.የደ/ብርሃን/ከ/አስ/ ፍትህ G+7 የቢሮ ግንባታ ስራ በከተማ በተመደበ በጀት ደረጃ 2 እና በላይ የሆኑ ጠቅላላ ስራ
ተቋራጭ /GC/ ወይም በህንፃ ሰራ ተቋራጭ/BC/ ፈቃድ ያላቸውን ተወዳዳሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትይፈልጋል።ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ
ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1, 2016 በጀት አመት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN / ያላቸው
3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነትየተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምስከር ወረቅት ማቅረብ አለባቸው፤
5. ተጫራቾች ከአማራ ከልል ውጭ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው ከሆነ የፌደራል የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዶች ጋር አያይዘውማቅረብ አለባቸው::
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው::
8. የግንባታ ስራውን ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
9.በጨረታዉ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል
10.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስብር 1000 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በየሎቱ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠየክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ኦሪጅናል ወይም በጥሬ ገንዘብ በስማቸውለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በሚል አድራሻ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለባቸው።
12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ቴክኒካልና ፋይናንሻል በማለት ለየብቻው በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታበደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል።
13. ጨረታው በጋዜጣ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማአስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ግዥ አፊሰሮች ቢሮ ይከፈታል። እለቱ የበዓል ቀን ከሆነበሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
14. አሸናፊው ተጫራች ውጤት ከተገለፀበት ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ ባሉት 5 ቀን ውስጥ የሚፈለጉበትንማስረጃዎች በማቅረብ ውለታ መፈፀም ይኖርበታል።
15.በጨረታ አሸናፊ የሆነ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ/10%/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያትዕዛዝ/ሲፒኦ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማሰያዝ ይኖርበታል።
16.መ/ቤቱ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መዋዋል ይችላል።
17.መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው::
18. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
19. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስ.ቁ 0116375610/ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ
ሰዓት በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና
ንብረት አስተዳደር ቡድን
