የጨረታ ማስታወቂያ
Debre Markos University (ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተመደበለት በጀት ለ2 አመት የሚቆይ የትላልቅ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎትግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከዚህ በታች ማለትም፡-
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተውየመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፤
2 የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50.000.00/ሀምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ
3. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊየሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፤
4. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲአስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1ኛ ፎት ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በዩኒቨርሲቲው ሂሳብ ቁጥር 1000017980517 ንግድባንክ ገቢ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
5. ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡ 59 ድረስ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት አለባቸው፤
6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀንከጠዋቱ 4:30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖምተጫራቾች በጨረታ ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታ ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታንጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይክፈታል፡፡
7. የጨረታውን ፋይናንሺያል ኦርጅናል ዶከመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተምበማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸው፡፡
8. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሣሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው
በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 058-771-6691 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
