የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 03/2016 ዓ.ም
National Alcohol and Liquor Factory (ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ)
ድርጅታችን ያገለገሉ የተለያዩ ወንበሮች፤ ጠረጴዛዎች, ሼልፎች፣ የቢሮ እቃዎችና ሌሎች በጅምላ ዋጋ በግልፅ ጨረታአወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ስመሳተፍ፡-
1. የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ፤
2. መካኒሳ ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ንብረቶችን ማየት ይቻላል፤
3. ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ የማይመለስ ቫትን አካቶ በብር 115.00 / አንድ መቶ አስራ አምስት ብር/ በመክፈልማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ ዋናው መ/ቤት ገንዘብ ቤት በመቅረብ መግዛትየምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
4. ዋጋ ማቅረቢያ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጅምላ ዋጋው ቫትንያካተተ መሆኑ ወይም አለመሆኑ መገለፅ አለበት፡፡
5. ለጨረታ ማስከበሪያ / ዋስትና / የሚሆን ብር 70,000 ( ሰባ ሺህ) በሲፒአ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
6. ዘወትር በስራ ቀን ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት መካኒሳ ዋናው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡10 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 0113690963 /0711460279
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
