የጨረታ ማስታወቂያ FHC/NCB/PG/43/10/2016
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሚያከናውነው የአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ስራ አገልግሎት የሚውልየቴራዞ ቀለም (ቀይ፣ ቢጫ፣ ብርቱካናማ እና ግራጫ) ወይም Terrazzo color (Red, yellow Orange & Grey) Iron oxide pigment ከአምራቾች ወይም አስመጪዎች በጨረታ መለያ ቁጥር FHC/NCB/PG/43/10/2016 በጨረታ አወዳድሮ ግዥመፈፀም ይፈልጋል፡
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ስራ አገልግሎት የሚውል የቴራዞ ቀለሞችግዥ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በአንድ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከናሙና ጋር ማቅረብአለባቸው፡፡
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል፡፡
4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀንጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀርበሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ወይም በተለምዶ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎበተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ወይም ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብአለባቸው፡፡ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደርዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች ግብዓቶችን ገላን ለሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የአርማታዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ያቀርባል፡፡
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር on-855-36-17 ወይም 011-553-95-35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
