የአማካሪ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዚ ቡድን
የጨረታ ቁጥር 008/2016
የአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ ቤት በክፍለ ከተማው በወረዳ 12 ገላንኮንዶሚኒዬም የጂ+4 ለጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ግንባታ ሙሉ የዲዛይን ስራ እና የጂ+3 ወጣት ማእከል፣የጂ+4 ት/ቤት እና የጂ+2 ላይብረሪ ስትራክቸራል ዲዛይን ስራ ሃገር በቀል አማካሪዎችን አወዳድሮ በማዋዋል ለማሰራትይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ስስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሱትንመስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
1. ደረጃቸው CAE (ኮንሰልቲንግ አርክቴክት ኢንጂነር) ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
2. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፣ ከኮንስትራክሽን ቢሮየልዩ ማማከር ስራ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውመጫረት ይችላሉ (ለ2016 ያሳደሱ)፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ ቤት 2ኛ ፎቅ ይህ የጨረታ ማስታወቂያበጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት የስራ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን ዋናና ኮፒ በመያ ዘወትር በስራቀንና ሰዓት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን፤
ሀ. ቴክኒካል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ
ለ. ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቬሎፕ እንዲሁም ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናትፖስታ በማሸግ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣከወጣበት ዕለት አንስቶ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሰረት በዚሁ ዕለት የጨረታሰነዱን (Technical and Financial) ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል፣ ኮፒዎቹ ላይ ኮፒ በማለት መጻፍ ያለባቸው ሲሆን፣ ይህንአለማድረግ ከውድድር ያሰርዛል፡፡
5. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(bid bond) 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በባንክዋስትና በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስይዙትንም (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦሪጂናል ዶክመንት ጋር አያይዘው ማቅረብ አለ
7. በአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ስራ ያላቸው የስራ ተቋራጮች በክ/ከተማው ጨረታ ለመሳተፍ የያዙትን ስራ ከ 70% በላይ ማድረሳቸውን መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. የጨረታውን መመሪያ አለማክበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
9. ከአንድ ሰነድ በላይ መወዳደር፣ ከተወዳደሩበት ሁሉ ላይ ያሰርዛል፤ በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
10. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
11. አድራሻ፡- ከቃሊቲ መነኻሪያ ፊት ለፊት በሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ህንጻ ላይ ሁለተኛ ፎቅ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን፡፡
12. ልዩ አማካሪው ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ቢያንስ የሰራተኛውን 40% በክፍለ ከተማው የተመዘገበ ስራ አጥ ባለሙያ ወይም መሃንዲስ መቅጠር አለበት፡፡ ለዚህም መተማመኛ በድርጅቱ ሃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡
13. አማካሪው ድርጅት የዲዛይን ማሻሻያ ስራ ይሰራል፡፡
14. አማካሪ ድርጅቱ ሥራውን በጥራት ለማከናወን የሚከተላቸውን መሰረታዊ _ ስትራቴጂዎች የሚያቀርብና _ እነዚህም _ ባለመፈጸማቸው ተጠያቂ እንደሚያደርገው ማረጋገጫ የጻፈና በስራ አስኪያጅ ወይም በሃላፊው የተፈረመና ማህተም ያለው ሰነድ የሚያቀርብ፡፡
15. ልዩ አማካሪው በደረጃው እንዲያሟላ የሚጠበቅበ ያለውና በህጋዊ መንገድ በከፍለ ከተማችን የተመዘገቡ የሚቀጥር መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ እንዲሁም ፕሮጀክቱን በጥራት ለማከናወን በቴክኒክ ሰነዱ ላይ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ባለሙያዎችን በወቅቱ እንደሚያሟላ በድርጅቱ ሃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
የምህንድስና ግዚ ቡድን
