የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ ሰይፈ ገ/ፃዲቅ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ገ/ፃዲቀ ጨርቆስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ ቤት በመ/ቁጥር 289626 በ21/3/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤ/ቁጥር አዲስ የሆነው የዋናው ቤት ስፋት 199.74 ካ/ሜ የሰርቪስ ቤቱ ስፋት 33.44 /ሜ የቦታ ስፋት - 233.18 ካ/ሜ መሆኑን በካርታ በውል የተፈቀደው ይዞታው ስፋት 175 ካሜ በገብረፃዲቅ ጨርቆስ ስም
የተመዘገበ ካርታ ያለው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 9,833,325 (ዘጠኝ ሚሊዬን ስምንት መቶ ሰላሳ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ አምስት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ7፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡፡ ከı/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው ይከፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
