የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
Stainless Steel pipe Z & C Purlin & Zamil steel structure Different Valves ۸۰۸۴ ጊዜ የወጣ እና ቁርጥራጭ ብረታብረት ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሽያጭ ግልጽ ጨረታ የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳየሚገኝ ሲሆን ፋብሪካችን የተለያዩ ዕቃዎችን
ማለትም፡-
በሎት .1। Stainless Steel pipe በሎት 2 Z & C Purlin & Zamil steel structure፤ በሎት3 Different Valves እና በሎት በሎት4 ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍትችላላችሁ፡፡
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው::
2. በጨረታው ተሳትፎ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ሙሉ ክፍያ ቅድሚያ ከፍሎ ማንሳትየሚችል መሆን አለበት፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶሰት መቶ ብር/ ብቻ በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካበኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000057735167 ገቢ በማድረግ አዲስ አበባ ካዛንችስ መናኸሪያ ሆቴል ጀርባበሚገኘው ቢሮአችን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀምሌ 09/2016 ዓ.ም ዘወትርበስራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለምትወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት 2% ፐርሰንት /ሁለት ከመቶ/ በባንክየተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.አ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጋራንቴ (ቢድ ቦንድ) በጣና በለስስኳር ፋብሪካ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብረው አያይዘው ማስገባት አለባቸው፡፡
5. በጨረታው የሚሳተፉ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን የጨረታና የውል ማስከበሪያ ዋስትና አያያዝን በተመለከተበአንድ ሎት የሚወዳደሩበት ጠቅላላ የመግዣ ዋጋ እስከ ብር 1,500,000.00 /አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ከሆነ ካደራጃቸው አካል ከተደራጁ አምስት ዓመት ያልሞላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እና የጨረታማስከበሪያ ዋስትና ድጋፍ ደብዳቤ በማጻፍ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብረው አያይዘው ማስገባት ይችላሉ፡፡ ሆኖም በአንድ ሎት የሚወዳደሩበት ጠቅላላ የመግዣ ዋጋ ከ 1,500,000.00/አንድ ሚሊዮን_ አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ከላይ በተ.ቁ. 4 በተገለፀው አግባብ መሰረት ተፈፃሚ የሚሆን ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ አስከ ሀምሌ 09/2016 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ዋና እና ቅጅ ዋጋ የተሞላበትን ኦርጅናል ሰነድ በአንድ ፖስታ ኦርጅናል በማለት ኮፒውን ደግሞ በሌላ ፖስታ ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ አዲስ አበባ ካዛንችስ መናኸሪያ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው ቢሮአችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ዋጋ የተሞላበትን አሪጅናል ሰነድ ኮፒ አድርጎ ለብቻ በፖስታ አሽጎ ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
7. ጨረታው በቀን ማለትም ሀምሌ 09-/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ካዛንችስ መናኸሪያ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው ቢሮአችን የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች በየሎቱ ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎችን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው አግባብ መሰረት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ ሀምሌ 09/2016 ዓ.ም ንብረቶቹ የሚገኝበት ፋብሪካ ድረስ በመምጣት ማየት ይችላሉ፡፡
9. ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ ተገልፆ ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ሳይሆን ከቀረ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለሁለተኛው አሸናፊ የሚሰጥ ሲሆን ሁለተኛው አሸናፊ የሚገዛበት ዋጋም አንደኛው በአሸነፈበት ዋጋ ይሆናል፡፡
10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-558-6725 ደውሉ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
