ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል
መከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ ደርሶ መልስ፣ በኦሮሚያ ብሄራዊክልላዊ መንግስት ቢሾፍቱ ከተማ ዙሪያ ደርሶ መልስ እና አዳማ ከተማ ድርሶ መልስ ለክፍሉ ሰራተኞች የሰርቪስ ▪ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን ለመከራየት አከራይ ድርጅቶችን አወዳድሮመከራየት ይፈልጋል፡፡
ዝርዝር መስፈርቶች በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳይ ይገስፃሱ፡-
1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት /ኦላይን/፤ የቫት/ ተጨማሪ እሴትታክስ ቲን/ነበር /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/፤ በጨረታ እንዲሳተፉ የሚገልፅ፤ የዘመኑ ግብር በአግባቡ የከፈሉመሆናቸውን የሚያረጋግጥ /ታክስ ክሊራንስ/ የተሽከርካሪዎችን ሊብሬና ሶስተኛ ወገን እና ሌሎችም ከጨረታው ጋርተያያዥነት ያላቸውን ዶክመንቶች ማቅረብ የሚችሉ የተጠቀሱትን ሰነዶች ማስረጃ ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነዳቸውጋር አያይዘው የሚያቀርቡና ዋናውን ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንን አስመልከቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ መሠረት ይሆናል፡፡
3. በመኪና ኪራይ አገልግሎት ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 (አራት መቶብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰንድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ሳጥኑ በ12/11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ12/11/2016 ዓ.ም ይከፈታል፡፡
6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆንበ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
7. በመኪና ኪራይ አገልግሎት ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 240,000.00 (ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር) ብቻ በመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት ቢሮ ቁጥር 136 እና ጨረታው የሚከፈትበት ሁለገብ አዳራሽ ቁጥር 1 ወይም ቁጥር 125
አድራሻ፡- ቢሾፍቱ ከተማ (ደብረ ዘይት) ቀበሌ 05 መከላከያ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አጠገብ መከላከያ/ስፔ/ሪፈ⁄ሆ/ል ስልክቁጥር 09-20-43-42-29/ 09-29- 19-08-52
የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል
