የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 46/2016
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
በጉምሩክ ኮሚሽን የሃዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰዉ የሚገኙ አንድ ገልባጭ መኪና፤የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ
ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታችየተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢየሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ 6 ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልሲሆን ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም፣
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓትከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡ 00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻየማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ::
3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርበታል፡፡
4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው)ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 የሚከፈት ሲሆንበሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይጀመራል፣ ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰዉ የሚገኙ አንድ ገልባጭ መኪና፤የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋበሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫት እና ያለቫት በሚል በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱለመቀበል አይገደድም፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይምማሻሻል አይችልም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤትእስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (03) የስራ ቀናት ውስጥ
የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
10. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው፡፡
12. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀናት ውስጥየአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙትየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 0462125396
ጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
