የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 3/2016
አፋር
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ልዩልዩ የቢሮ መገልገያዎች ሽያጭ
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማ 3 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችንና ልዩልዩ የቢሮ መገልገያዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታአወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስስዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች -
1. የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው በአ/ማሕበሩ አድራሻ በግንባር በመገኘት የማይመለስብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
2. ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስኪከፈት ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜውስጥ ተሽከርካሪዎቹን አውራሪስ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው በኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ግቢእንዲሁም የቢሮ መገልገያዎችና ፈርኒቸሮችን ካፒታል ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኢ ማሕበሩ ዋና መ/ቤት በመምጣትባለበት ሁኔታ መመልከት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች ለሚገዟቸው ተሽከርካሪዎች እና ልዩልዩ የቢሮ መገልገያዎች የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ ኦ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል:: የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊ ለሆኑት በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ይታሰብላቸዋል፡፡ ለተሸነፉትተመላሽ ይደረጋል፡፡
4. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው::
6. በመሆኑም ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሠነዶቻቸው ላይ የድርጅታቸውን ስም ፤ የጨረታውን ዓይነት፤ ሙሉአድራሻቸውን፤ ስልክ ቁጥራቸውን እንዲሁም ኢ- ሜላቸውን አስፍረውና ፈርመው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
7. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ አይነትና ዋጋ በቁጥርና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአ/ማሕበሩ ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስማስገባት አለባቸው::
8. ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል፡፡
9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-618 70 69 ወይንም 011-618 7068 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
10.ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ሃያ ሁለት ከካፒታል ሆቴል ጀርባ ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ አጠገብ
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማሕበር
