የግልጽ ጨረታ ማስታዎቂያ የጨረታ ቁጥር አህስኮድ ማሽግ/08/2016)
የአማራ ሕንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጋራዥ አገልግሎት የሚውል መፍቻ (ቱልስ) እና የተለያዩ ጎማዎችህጋዊ ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታውለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስየምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፡፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም (Unconditional bank guarantee) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ አማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 እና አዲስ አበባ ለገሀርአካባቢ በሚገኘው አመልድ ኢትዮጵያ ህንፃ የአህስኮድ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4.የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎችበጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ( 15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባ/ዳር በሚገኘው በድርጅቱ የማሽ/ተሽ/ግዥና አቅ/ኬዝ/ቲም ቢሮ ( ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንፃ አካባቢየቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይርባቸዋል፡፡
5. ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ቦታ በ8፡00 ሠዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀንካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 8:00 ሠዓት ሳጥኑታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።
6. ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን እና የውል ይዘቱን በሙሉ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውምተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለበት፡፡
7.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር
ባ/ዳር:-0583205185/0918784490/0918715641
አዲስ አበባ :- 0111265652/0913158074
የአማራ ሕንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
