Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ከጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0113659360
  • Website
  • Deadline25 Jun 2024, 4:21 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድልማት ቢሮ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችን/ድርጅቶች /በክልሉ በሚገኙ ፣ ቡታጂራ፣ ሀላባ 9.ተ የዱራሜ ፣ ሙዱላ፤ ላጃ፣ ወራቤ እና ቆሼ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያዎችንአወዳድሮ የኢ-ትኬቲንግ አገልግሎት ማስጀመር ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ይዞ መቅረብ የሚገባቸዉ መረጃዎች፡-

1. የዓመቱን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

2. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው

3. ቴክኖሎጂውን ያበለፀገ ስለመሆኑና የፈጠራ ባለቤትነት ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ማቅረብየሚችል፣

4 ከመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር (NSA)የድጋፍ ደብዳቤ ያለው፤

5. ከዚህ ቀደም በታወቁ መንግስታዊ ወይም በውጭ ድርጅቶች በዘመናዊ ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ አገልግሎት የሰጡ _ ስለመሆናቸው ዕውቅና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡

6 ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችል፤

7. ዘመናዊ መናኸሪያን በቴክኖሎጂ በመገንባት በክልላችንም ሆነ በሌሎች ክልሎች የስራ ልምድ ወይም መልካም ምስክርነትያለው፡፡

8.በቢሮው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮው የግዥ ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብየማይመለስ 100 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤

9.ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያበአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ተከታታይ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 በፊት ብቻ ይሆናል ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀነ በ8፡30 ተዘግቶ በዚህ ዕለት በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አድራሻ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌዴሪ / በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

10. የጨረታ ማስከበሪያ /cpo/ 100,000.00/መቶ ሺህ ብር በማስያዝ የሚችሉ ሆኖ ፣ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል ፡፡

11. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 0991415433 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የቢሮው አድራሻ፡- የወልቂጤ የዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡

የማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ

Save Tender