የጨረታ ማስታወቂያ
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሚያከናውነው የአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸው ግብዓቶች ማለትም የወንዝ አሸዋ እና ጠጠር ባለ (oo፣ 01 እና 02) አዲስ አበባ ገላን በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ሳይት ድረስ ከሚያቀርቡለት አምራቾች ወይም አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ በጨረታ መለያ ቁጥር FHC/NCB/PG/41/10/2016 ለሁለት ዓመት በሚቆይ የማዕቀፍ ስምምነት የግዥ ዘዴ በአጭር ግዜ ውስጥ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸው ግብዓቶች ማለትም የወንዝ አሸዋ እና ጠጠር (00፣ 01 እና 02) ግዥ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልከቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል፡፡
4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀረ በሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ወይም በተለምዶ የስነ- ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ወይም ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች ግብዓቶችን ገላን ለሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ሳይት እና እንደአስፈላጊነቱ በስሩ ለሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያቀርባል፡፡
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-855-36-17 ወይም
011-553-95-35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
