Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Jun 2024, 11:09 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


በፍ/ባለመብት ሲስተር እቴቱ ከበደ እና በፍ/ባለዕዳ የማታወርቅ ተፈራ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 306615 በ18/11/2015 ዓ.ም እና መ/ቁ 313721 በ29/2/2016 ዓ.ም በ15/9/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤ.ቁ 592 የቤቱ ስፋት 67 ካ/ሜ በንፅፅር የሚደርሰው የቦታው ስፋት 54 ካ/ሜ ጠቅላለ የቦታው ስፋት 121 ካ/ሜ ሲሆን የይዞታው መለያ ቁጥር AA000030900470 በእነ ሲስተር እቴቱ ከበደ ገብርስላሴ ስም ተመዝግቦ የሚገኝው ቤት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ በፌ/ፍ/ፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት በሚል CPO 2,298,412.25 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አራት መቶ አስራ ሁለት ብር 25/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ አሁን የሚሸጠው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 428 (1) መሰረት ነው:: የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከı/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender