ባቄላ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ መጠኑ 3,065.15 ኩ/ል ባቄላ በአዳማ እና ኢተያመጋዘን የሚገኝ ሲሆን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው
ድርጅቶች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ/ቁ |
እህል የሚገኝበት ቦታ |
የእህል አይነት |
መጠን በኩ/ል |
የጥራት ደረጃ |
እህሉ የሚገኝበት መጋዘን |
እህሉ የሚውለው አገልግሎት |
|
1 |
አዳማ |
ባቄላ |
1,420.18 |
1ኛ ደረጃ |
09 |
ለሰው ምግብነት |
|
2 |
ኢትያ |
ባቄላ |
1,644.97 |
1ኛ ደረጃ |
045 |
ለሰው ምግብነት |
|
ድምር |
|
3,065.15 |
|
|
|
|
1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በጅምላና ችርቻሮ ንግድ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
2. ባቄላውን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮዘወትር በስራ ቀናት ባቄላው በሚገኝበት መጋዘን በአዳማ እና በኢተያ መጋዘን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብጠዋት 2፡00 - 6፡00 እና ከሰዓት 7፡00 – 10፡30 እና ቅዳሜ ከ 2፡00 - 6፡00 የክምችቱን ሁኔታ በአካል ቀርበው ማየትይችላሉ፣
3. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት (አዲስ አበባ) ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛትይችላሉ፤
4. ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በዘርፉ ስም (የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ ወይም Grain and Coffee Trading Business Unit) በሚል ብቻ የተሰራ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፤
5. በግልፅ የማይነበብ ትከከለኛውን የዋጋ አቀራረብ ሥነ ስርዓት ያልተከተለ የመጫረቻ ሠነድ ውድቅ የሚደረግ ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ ስርዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ያስፈልጋል።
6. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ሰነዳቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥር 03/2016 በማለት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአሰራ እንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 302 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ባለው ቀን ይሆናል።
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ፤ አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ባለው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 311 በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
8. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
9. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት እህሉን ተረክቦ ወደሚፈልግበት ቦታ በራሱ የሚያጓጉዝ ይሆናል ።
10. ዘርፉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ ሙቡቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 4 66 47 45 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤
በኢትዩጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ
