የግልጽ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ አልባሳት፣ ጫማ ፣ የቤትዕቃ ፣ እስፔርፓርት፣ ምግብ ነክ፣ ኮንስትራክሽን፣ የፅዳት ዕቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅና ሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎችን ዘ/10/2016 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
ስስሆነም በጨረታው ሳደ ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-
1. በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
2. ሀራጅ ጨረታ በመሳተፍ እቃዎቹን ለመግዛት 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
3. ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ዕቃዎቹን ለመግዛት የሚቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቀረብ የሚችል፤
4. ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
6. ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ከፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
7. ዕቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በዐ5 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው (ሲ.ፒ.ኦ) (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፤
8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመስላቸዋል፤
9. ማንኛውም ተጫራች የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) አሰርቶ ማምጣት አለበት፤
10. አሳማኝ የሆነ ምከንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
11. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
12. ተጫራቹ ዕቃቆችን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
13. ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ በ14/10/2016 ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3፡45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው 3:45 ተዘግቶ በ13/10/2016 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
14. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው 14/10/2016 ከረፋዱ 4:30 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
N.B:- አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም::
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
