የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ ህፃን በሀይሉ አለማየሁ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ዝናሽ ደቻሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይየፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/138669 በ20/05/2007 ዓ/ም እና በኮ/መ /ቁ/166161~18/7/2007 ዓ/ም በ 30/9/2015 9/23/4/2016/ በዋለውችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር1988 የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 16,872,250 (አስራ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ሁለትመቶ ሃምሳ ብር) በቁጥር ቦሌ 01/285/6715/00 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት 250 ካ/ሜ የትራንዛክሽን ታክስገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮየቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ንብረቱን ተጫርተው ለመግባት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍልድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታውአይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀንጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግአለበት፡፡ የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
