የጨረታ ማስታወቂያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ተለያዩ ተቋማት ለሚያቀርበው የሰው ኃይል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩየደንብ ልብሶችን ማለትም የድርጅት ዓርማ (Logo) ያለባቸው የደንብ ልብሶች (ጃኬት፣ ሱሪ እና ቲ-ሸርት) ማቅረብየሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰምበታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግእንድትወዳደሩ ይጋብዛል::
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል::
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥእስከ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ያሸነፈው ተጫራች የዕቃዎች
ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ ግምጃ ቤት ይሆናል:: ከላይ የተጠቅሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራችያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል::
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሴ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው
የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
